Bulgaria mazoria, Addis Ababa, Ethiopia
info@eta.gov.et
ETA
Ethiopian Technology Authority
Home
About ETA
Services
Radiation sector
Industrial sector
Resources
ETA Publications
ETA Regulation
Others
News & Events
Latest News
Latest Event
Vacancy
Contact us
About Ethiopian Technology Authority
The Ethiopian Technology Authority (ETA) is a government organization established by Proclamation No. 1263/2021 to ensure the safety of the people, the environment and property from harmful effects of technology use and application in various industries and development sectors. The Authority has duties and responsibilities of regulating technology uses in industries with set regulatory standards and requirements at a level that make public safety certain, protect property damage and the environment from pollution while striking a balance between the desire to reduce technology use risks and the aspiration to put up with economically and socially productive activities. The typical technology focal sectors the Authority regulates include technologies that fall under radiation and nuclear, chemical, electronics and electric appliance, plant and machinery, material technology, emerging technology, aerospace and space technologies.
The Authority, accordingly, is mandated to regulate the aforementioned sectors technology uses. As its duties and responsibilities it issues licenses and licenses grades for activities related to the technologies, renews suspends and revokes licenses, carries out inspection on technology uses and takes appropriate measures when necessary. It also establishes an environmental monitoring system for chemicals use and procedures for enforcing and regulating the import and export of technologies or related practices and issues standards for regulated technologies. It performs other regulatory activities such as designing and implementing a systematic procedure for the implementation of the regulatory activities with regard to the mass media and other concerned bodies, establishing regulatory laboratory, cooperating with relevant national and international organizations, and formulating emergency preparedness and response plan for technological accidents and risks.
The Authority pays every possible effort to meet the objectives provided for in the establishment regulation regardless of the costs it may take, thus a desired level of technology use protection will be achieved.
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን (Ethiopian Technology Authority) በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ሲሆን የተቋቋመበት ዓላማም ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በኢንዱስትሪዎችና የልማት ዘርፎች ውስጥ ጥቅም ላይ ሲውሉ በህብረተሰቡ፣ ንብረትና አካባቢ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን የጎንዮሽ ጉዳት መቆጣጠርና የህብረተሰብን ንብረትንና አካባቢን ደህንነት ማረጋገጥ ነው፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎችና የልማት ዘርፎች ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ የሚውሉ ቴክኖሎጂዎች ከሚሰጡት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎት ባሻገር የጎንዮሽ ጉዳት እንዳያደርሱ የመቆጣጠር ስልጣንና ተግባር በህግ የተሰጠው ሲሆን የቁጥጥር ስራውን የሚተገብረውም በተቀመጡ የቁጥጥር ስታንዳርዶችና አስገዳጅ መስፈርቶች (set regulatory standards and requirements) መሰረት ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስራው ገቢራዊ የሚሆነው በሚፈለገው ደረጃ ህብረተሰብ፣ ንብረትና አካባቢ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስርዓት የጎንዮሽ ጉዳት መጠበቃቸውንና ደህንነታቸውን በማረጋገጥ ሲሆን እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለተለያዩ በጎ ዓላማዎች ጥቅም ላይ ሲውሉ የሚያበረክቱትን አገልግሎት ግምት ውስጥ በማስገባትም ይሆናል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በህግ በተሰጠው የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስልጣን መሰረት በኢንዱስትሪዎች ወይም የልማት ዘርፎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉና ቁጥጥር የሚያደርግባቸው የቴክኖሎጂ ውጤት ዓይነቶች ውስጥ የጨረራና ኑክሌር ቴክኖሎጂዎች፣ ኬሚካል ቴክኖሎጂዎች፣ ኤሌክትኒክ ዕቃዎች (electrical equipment)ና ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች (electronics devices)፣ ማሽነሪዎች (plant and machinery)፣ ቁሳካላዊ ቴክኖሎጂዎች (material technologies)፣ በቃይ ቴክኖሎጂዎች (emerging technologies) እና የስፔስ ቁሶች (aerospace and space technologies) ይጠቀሳሉ፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ከላይ በዘርፍ የተዘረዘሩትን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ፣ ወደ ተግባር እንዲገቡና ስራ ላይ በዋሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይም በህግ በተሠጠው ስልጣን መሰረት የቁጥጥር ስራዎችን ያከናውናል፡፡ በባለስልጣን መ/ቤቱ የዘርፍ ቁጥጥር ስር የሚወድቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ በአስፈላጊው የቁጥጥር ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ በማድረግ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ረገድ የተግባር ፈቃድ ይሰጣል፣ ከቴክኖሎጂዎች ባህሪ ጋር የተናበበ የፈቃድ ደረጃዎችን በመወሰን ፈቃድ ይሰጣል፣ የፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት ይሰጣል፣ ፈቃድ እንዲታገድ ያደርጋል፣ ፈቃድ ይሰርዛል፣ የዘርፍ ቴክኖሎጂዎች በተቀመጡ ስታንዳርዶችና መስፈርቶች መሰረት ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን ለማረጋገጥ የቁጥጥር ስራዎችን ያከናውናል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በህግ ከተቀመጠ አሰራር ውጭ የተከናወኑ ተግባራት ሲገኙ ለተፈጸሙ ስህተቶች ማስተካከያ የሚሆኑ ተመጣጣኝ ህጋዊ ርምጃዎችን ይወስዳል፡፡ የኬሚካል ቴክኖሎጂ ውጤቶች ጥቅም ላይ ሲውሉም በአካባቢ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ብክለት ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት የመዘርጋትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡና ወደ ውጭ የሚላኩ የኬሚካል ቴክኖሎጂዎችና ሌሎች ተዛማጅ ተግባራት አሰራር ቁጥጥር ህጋዊ ተፈጻሚነት እንዲኖረው የአሰራር ቅደምተከተሎችን (procedures) የማዘጋጀት ሚና አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በብዙሃን መገናኛና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጥቅም ላይ የሚውሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ቁጥጥር ስራን የሚያቀላጥፉ ቅደምተከተላዊ ስርዓቶችን (systematic procedures) የመንደፍና የመተግበር ስራዎችን ያከናውናል፡፡ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ላቦራቶሪዎችን የማቋቋም፣ አግባብነት ካላቸው የሀገር ውስጥና አለምዓቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በቴክኖሎጂ ቁጥጥርና ተዛማጂ የስራ ዘርፎች ዙሪያ በትብብር የመስራትና የቴክኖሎጂ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ የድንገተኛ አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ ዕቅዶችን የማዘጋጀት ተግባራትን የቁጥጥር ስራው አካል በማድረግ ተፈጻሚ ያደርጋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ዓላማዎችን ለማሳካት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ በመክፈልና በሙሉ አቅሙ በመንቀሳቀስ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስራው ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፡፡