Bulgaria mazoria, Addis Ababa, Ethiopia
info@eta.gov.et
ETA
Ethiopian Technology Authority
Home
About ETA
Services
Radiation sector
Industrial sector
Resources
ETA Publications
ETA Regulation
Others
News & Events
Latest News
Latest Event
Vacancy
Contact us
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስራዎች (Chemical Technology Regulatory)
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ በኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስር ከሚገኙ ስራ አስፈፃሚ አንዱ ሲሆን ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ላይ ሲውል በሰው፤ በእንስሳት ጤና ፤ በአካባቢ ደህንነት እንዲሁም በወደፊቱ ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሳያስከትል ቴክኖሎጂው ለዘላቂ ሃገራዊ ልማትና እድገት ለሚያበረክተው አስተዋፅኦ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የሬጉላቶሪ ቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን ለማከናወን የተቋቋመ የስራ ክፍል ነው፡፡ የኬሚካል ቴክኖሎጂ ሬጉላቶሪ ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ ሁለት ክፍሎች/ዴስክ ሲኖሩት አነሱም ፡
1. የኬሚካል ቴክኖሎጂ የማሳወቅና ፈቃድ አሰጣጥ ዴስክ
2. የኬሚካል ቴክኖሎጂ ኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈፀም ዴስክ
የኬሚካል ቴክኖሎጂ የማሳወቅና ፈቃድ አሰጣጥ ዴስክ
የኬሚካል ቴክኖሎጂ የማሳወቅ የስራ ድርሻ
ደንበኞች የኬሚካል ቴክኖሎጂን ለመትከል/install፣ ለማምረት፣ ለመጠቀም፣ለማጓጓዝ፣ ለመሸጥ፣ ለማዉረስ፣ ወደ ዉጪ ለመላክ፣ ወደ ሀገር ለማስገባት ስራ ከማስጀመራቸው በፊት ለባለስልጣኑ መ/ቤቱ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ደንበኞች የኬሚካል ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ወይም ከሀገር ለማስወጣት ለባለስልጣኑ መ/ቤቱ ሲያሳወቁ የሚከተሉትን መርጃዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በድርጅቱ ስም የተጻፈ ማመልከቻ ደብዳብ /Application Letter/
የማመልከቻውን ቅፅ (AP-NT-01 form)
የታደሰ የንግድ ፍቃድ
የብቃት ማረጋገጫ
የኬሚካሉን ጠቅላላ በህሪ የሚገልፅ ቅፅ ከአምራች ድርጅት የሚሰጥ(MSDS)
የኬሚካሉን የማጓጓዣ ሰነድ/ Shipping Documents/
ለተለያዩ የኬሚካል ቴክኖሎጂዎች የሚተከልባቸውን ክፍሎች ዲዛይን
የቀረበዉን የደንበኛ ሰነድ ከኬሚካል ደህንነት/safety/፣ ጥበቃ/security/ና የሴፍጋርድ/sefgaurds/ አንፃር ኢትዮጵያ የፈረመችዉን ኬሚካልን ለጦርነት አላማ ለመጠቀም ማበልፀግ፣ ማምረትና ማከማቸት የሚከለክል ኬሚካል ዊፐን ኮንቬንሽን/ Chemical Weapon Convention/CWC/ የስምምነት ሰነድንና ሌሎች የሀገሪቱን ደንብ እና መመሪያዎችን መሰረት ያደረገ መሆኑን ተከታትሎ ተገቢዉን ዉሳኔ ይሰጣል፡፡
ለባለድርሻ አካላቶች ወይም ከባለስልጣናቱ መ/ቤቱ በጋረ ለሚሰረሩ ተቋማት ሰራተኞች የክህሎት ክፍተት በመለየት ክፍተቱን ለመሙላትና የመፈጸም አቅማቸውን ለማጎልበት የሚረዳ አጫጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡
ኬሚካል ቴክኖሎጂ ፈቃድ አሰጣጥ የስራ ድርሻ
ተቋማት ለኬሚካል ቴክኖሎጂ ተግባራት ፈቃድ ሲጠየቁ የፈቃድ መጠየቂያ ደብዳቤ፣ የሰራተኞች የሙያ ፈቃድ፣ የሰራተኞች የኬሚካል ብክለት መከላከያ የሴፍቲ አልባሳት/Chemical protective equipments/፣የጥራት ማረጋጋጫ ስርዓት(Quality Assurance) ፕሮግራም፣ የድንገተኛ አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ እቅድ አሟልተዉ ማቅረባቸዉን እንዲረጋገጥ በማድረግ ተገቢዉን ዉሳኔ ይሰጣል፡፡
ተቋማት የኬሚካል ቴክኖሎጂ ለማምረትና ለመጠቀም ፈቃድ እንዲሰጠቸዉ የአካባቢ ተጽዕኖ የግምገማ (Environmental Impact Assessment) ሰነድ በሰይንሳዊ ዘዴ መተንተኑንና ለተቋሙ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የማሳወቅ ስርዓትን አልፎና ከላይ የተጠቀሱትን የፈቃድ መስፈርቶች ለአሟሉ ተቋማት የፈቃድ ጥያቄ / እድሳትን በተገቢው ሁኔታ በማረጋገጥ ለሚከተሉት የፍቃድ አይነቶች / እድሳት ይሰጣል፡፡
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ወድ ሀግር ውስጥ ማስገባት ለሚፈልጉ አካላት ፈቃድ መስጥት
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ከአገር የማሰውጣት ጥያቄ ሲቀርብ ባለስልጣኑ ከአገር እንዲወጡ ፈቃድ ይሰጣል
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ሲቀርብና በባለስልጣኑ ቁጥጥር መነሻነት የተግባር ፈቃድ መስጠትና ማደስ
የኬሚካል ቴክኖሎጂ አከፋፋዮች፤አገልግሎት ሰጪዋች የብቃት ማረጋግጫ ፈቃድ መስጠት/ ማደስ
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈፀም ዴስክ
የኬሚካል ቴክኖሎጂ የኢንስፔክሽን የስራ ድርሻ
የኬሚካል አምራችና ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት ኬሚካል ቴክኖሎጂ ሲመረት፣ ጥቅም ላይ ሲዉል፣ ሲከማች፣ ሲጓጓዝና በሰራተኛ፣በማህበረሰቡ፣ በአካባቢና ንብረት ላይ የጎንዮሽ ተፅኖ እንዳያደርስ በተዘጋጁ መመሪያዎችና መስፈርቶች መሰረት ተግባራዊ መሆናቸዉን በመደበኛና ድንገተኛ እንደ ኬሚካል አደገኝነት ባህሪያችው ኢንስፔክሽን በአካል በቦታዉ(በፋብሪካ፣ በህክምና ተቋማት ወዘተ) በመገኘት ያረጋግጣል፡፡
ተቋማት ከኬሚካል ደህንነት/safety/፣ ጥበቃ/security/ና የሴፍጋርድ/sefgaurds/ አንፃር ኢትዮጵያ የፈረመችዉን ኬሚካልን ለጦርነት አላማ ለመጠቀም ማበልፀግ፣ ማምረትና ማከማቸት የሚከለክል ኬሚካል ዊፐን ኮንቬንሽን /CWC/ የስምምነት ሰነድንና ሌሎች የሀገሪቱን ደንብ እና መመሪያዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ ስራቸዉን እያከናወኑ መሆናቸዉን በመደበኛና ድንገተኛ ኢንስፔክሽን እንዲረጋገጡ ያደርጋል፣ ተግባሩን ይከታተላልል፡፡
የኬሚካል ቴክኖሎጂ አምራቾች ፣ ተጠቃሚዎችና አጓጓዦች ሰራተኞች የኬሚካል መከላከያ አልባሳትና ቁሳቁሶች /Chemical protective equipment/ መሟላቱን ያረጋግጣል፡፡
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ሕግ ማስፈፀም የስራ ድርሻ
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ደንብ፣ መመሪያዎች፣ የሬጉላቶሪ መስፈርቶች ከማያሟሉ ተቋማት ጋር በተያያዘ አስተዳደራዊና ሕጋዊ የህግ ማስፈፀም እርምጃዎች ይወስዳል፡፡
በመደበኛና ድንገተኛ ኢንስፔክሽን የተገኙ የተጓደሉትን መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ አስተዳዳራዊና ህጋዊ የህግ ማስፈፀም እርምጃ እንደየ ጉድለቱ ደረጃቸው የሚወሰዱ ሲሆን በዋናነት ፡- የቃል ማስጠንቀቂያ ፣ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ የመጨረሻ ጊዜ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ የተቋማት እሸጋት፣ የገንዘብ ቅጣት፣ የስራ ፍቃድ ማገድና፣ ስራ ፈቃድ መንጠቅ፣ እስራት ይሆናል
ተከሰዉ በፍርድቤት ክትትል ላይ ያሉ ተቋማትን ዉሳኔ ይከታተላል፣ ዉሳኔዉ ፍታዊ ካልሆነና ይግባኝ ካስፈለገ የሚቀርቡ ሃሳብ ገምግሞ ያፀድቃል፣ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፡፡
የኬሚካል ቴክኖሎጂ ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ መዋላቸዉን ያረጋግጣል ነገር ግን ከሰላማዊ አገልግሎት ዉጪ ሊዉሉ የሚቺሉ የኬሚካል ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚዎች ህጋዊ እረምጃ ይወስዳል፡፡