Director General's Message
Technology refers to the application of scientific knowledge for practical purposes by industries and various development sectors. These-days technology has continued to emerge at a phenomenal rate. It has made great progress in its application not only in daily life but also in medical fields. Evidently, its application has aided civilization in a variety of ways, the most notable of which are health care, education and communication. We can confidently speak that society and technology are inextricably linked. Despite the fact that technology is the great enabler, reliance on technology,
however also presents potentially high-impact risk on the public, environment and property in situations where proper safety and security precautionary measures are not taken. Its application can potentially be harmful if used wrongly and can also undermine societal safety and worsen environmental pollution. Exposure to ionizing radiation can cause health problems such as immediate damage to a person's body, radiation sickness, cardiovascular disease, cataracts, cancer as well as death. Chemical technologies have the potential to weaken the immune system, can cause development of allergies or asthma, reproductive problems, birth defects and bring effects on the mental, intellectual or physical development of children. Nowadays electronic devices are becoming more widely used particularly by young people but little consideration is normally given to the health risks they pose. Recent developments in the use of material and emerging technologies raise concerns which may come up with unforeseeable obstacles that can cause considerable damage to the public in different ways. Aerospace and space technologies applications in satellite imagery, satellite communications and similar practices, if left free-for-all, can still have risks to the society and its environs. The cited technology application related safety and security problems need to be regulated by a competent public body. The Ethiopian Technology Authority established by proclamation No. 1263/2021 is a public regulatory body mandated to regulate technology uses in industries with set regulatory standards and requirements at a level that make public safety certain, protect property damage and the environment from pollution while striking a balance between the desire to reduce technology use risks and the aspiration to put up with economically and socially productive activities. Legal and regulatory responses help tackle the range of risks and harms that threaten public safety and security issues that may arise from technology applications. Establishing laboratories is also at the heart of technology regulatory functions. Robust awareness programs on safety and security measures related to technology use and regulatory functions are essential for ensuring public support where this basically requires engaging stakeholders and partners at local and international levels. To fulfil the growing demand of technology use regulation, the authority pays every possible effort to meet the objectives provided for in the establishment proclamation regardless of the costs it may take, thus a desired level of technology use risk protection will be achieved.
ቴክኖሎጂ የሚለው ቃል ሲገለጽ ሳይንሳዊ ዕውቀትን በኢንዱስትሪዎችና ልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች ለተለያዩ ተግባራትና ዓላማዎች ጥቅም ላይ መዋልን የሚያመለክት ጽንሰ-ሃሳብ ነው፡፡ በአሁኑ ዘመን ቴክኖሎጂ ክስተት በሚመስል መልክና በሚያስደንቅ አኳኋን በገፍ በመፈጠር ላይ ይገኛል፡፡ ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ የማዋል ሂደት ከፍተኛ መሻሻሎችን እያስመዘገበ የመጣ ሲሆን ይህ ዕድገት በቀን ተቀን የሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ብቻ የሚስተዋል ሳይሆን በህክምናው ዘርፍም እንዲሁ በሰፊው ጥቅም ላይ መዋል ችሏል፡፡ ቴክኖሎጂ በፈርጀ-ብዙ መልኩ ጥቅም ላይ መዋል መቻሉ የሰው ልጅ ስልጣኔን ያሳለጠ ሲሆን በዋናነት በጤና አጠባበቅ ትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፎች ላይ ያመጣቸውን ለውጦች በማስረጃ ማሳየት ይቻላል፡፡ ማህበረሰብና ቴክኖሎጂ ላይለያዩ የተጣመሩ በሚመስል መልኩ የተጋመዱ ስለመሆናቸው በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ቴክኖሎጂ ምንም እንኳ በሰው ልጂ ኑሮ ውስጥ ወሳኝ የአስቻይነት ሚና ቢኖረውም ለተለያዩ ዓላማዎች ጥቅም ላይ ሲውል አስፈላጊው የደህንነት ጥንቃቄ ርምጃ በተቀመጠ የቁጥጥር አሰራር ቅደምተከተል ህግና መስፈርት መሰረት ካልተወሰደ በህዝብ አካባቢና ንብረት ላይ ሊያስከትል የሚችለው አደጋ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ጥንቃቄ በጎደለው አግባብ ጥቅም ላይ እንዲውል ከተደረገም የማህበረሰብን ደህንነት ጥያቄ ውስጥ ከማስገባቱም በላይ የአካባቢ ብክለትን ሊያባብስ ይችላል፡፡ ጨረራን ለሚያመነጩ ቴክኖሎጂዎች ባልተገባ መንገድ መጋለጥ በሰዎች አካል፣ ቆዳ፣ ልብና አይን ላይ ካንሰርን ጨምሮ ጉዳት የሚያመጣ ሲሆን ሞትንም ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለኬሚካል ቴክኖሎጂዎች ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ መጋለጥ ደግሞ የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም የማዳከም፣ ለአለርጅ ወይም አስም በሽታ መጋለጥን፣ በመራቢያ ስርዓቶች ላይ ችግር መከሰትን፣ አካላዊ ጉድለት ያለባቸው ልጆች መወለድንና በልጆች አዕምሮ፣ የትምህርት አቀባበል ወይም አካላዊ ዕድገት ላይ ችግሮችን ያስከትላል፡፡ ዛሬ ላይ ምንም እንኳ በጤና ላይ ሊያመጡ የሚችሉት አደጋ ብዙ ትኩረት ባይሰጠውም የኤሌክትሪክ ፍሰትን በመቆጣጠር የመረጃ ፍሰትንና መስተጋብርን የሚያሳልጡ መሳሪያዎች በስፋት ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ፡፡ ቁሳካላዊ እና በቃይ የቴክኖሎጂ ዘርፎችን ጥቅም ላይ በማዋል ሂደት እየታዩ ያሉ አሁናዊ ዕድገቶች መተንበይ የማይቻሉ የደህንነት ችግሮችን ሊያስከትሉ የሚችሉ በመሆኑ ስጋትን መደቀናቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ የሰው ልጅ የኤሮስፔስ ቴክኖሎጂንና የስፔስ ቁሶችን የሳተላይት ምስል ለመውሰድ፣ በሳተላይት የታገዘ የኮሙዩኒኬሽን ስርዓት ለመከወንና ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ለማከናወን የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከቁጥጥር ነጻ ከሆኑ በህዝብና አካባቢ ላይ አደጋን ያስከትላሉ፡፡ ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱት የቴክኖሎጂ ዘርፎች በአጠቃቀም ጉድለት በደህንነት ላይ ችግር እንዳያስከትሉ በህግ የተቋቋመና ብቃት ያለው መንግስታዊ ተቆጣጣሪ አካል ማቋቋም ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1263/2021 መንግስታዊ ተቋም ሆኖ የተቋቋመውም ለዚሁ የቁጥጥር ዓላማ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎች ጥቅም ላይ ሲውሉ በተቀመጡ የቁጥጥር ስታንዳርዶች እና መስፈርቶች መሰረት በኢኮኖሚው ዘርፍና ልማት እንቅስቃሴዎች ዘንድ የሚያበረክቱትን በጎ አስተዋጽኦ ግምት ውስጥ ባስገባ አግባብ የህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ የንብረት ውድመትን ለመከላከልና አካባቢን ከብክለት ለመታደግ የቁጥጥር ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ህጋዊ ርምጃ በመውሰድና የቁጥጥር ስራዎችን በማከናወን በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሂደት የሚያጋጥሙ አደጋዎችን፣ ጉዳቶችንና በህዝብ ደህንነት ላይ ስጋት ለሚደቅኑ ዘርፈብዙ ችግሮች ምላሾችን መስጠት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ይጠበቃል፡፡ የቁጥጥር ስራዎችን የሚያሳልጡ የላቦራቶሪ መሰረተ-ልማቶችን ማደራጀት ደግሞ አንድ የቁጥጥር ስራው ዋና ጉዳይ ሆኖ ይወሰዳል፡፡ የተጠናከረ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ዓላማና ተልዕኮ እንዲሁም የደህንነት ርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊነትን የተመለከቱ የግንዛቤ ማስፊያ ፕሮግራሞችን ማካሄድ በቁጥጥር ስራዎች ትግበራ ላይ የህዝብ ድጋፍ የሚያስገኝ ሲሆን ይህ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆንም በሀገር ውስጥና አለምዓቀፍ ደረጃ የሚገኙ ባለድርሻዎችንና አጋሮችን ማሳተፍ ያስፈልጋል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በቴክኖሎጂ ቁጥጥር መስክ በዓይነትና ቁጥር እየጨመረ ለመጣው የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በህግ በተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት መሰረት የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል ሀላፊነቱን ይወጣል፡፡