Bulgaria mazoria, Addis Ababa, Ethiopia

info@eta.gov.et

ETA logo ETA Ethiopian Technology Authority
  • Home
  • About ETA
  • Services
    • Radiation sector
    • Industrial sector
  • Resources
    • ETA Publications
    • ETA Regulation
    • Others
  • News & Events
    • Latest News
    • Latest Event
    • Vacancy
  • Contact us

የጨረራና ኒዩክሌር ቴክኖሎጂ ማሳወቅና ፈቃድ አሰጣጥ

የጨረራና ኒዩክሌር ቴክኖሎጂ ማሳወቅና ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ በሁለት ዴስኮች የተዋቀረ ሲሆን አንዱ የፈቃድ አሰጣጥ ሲሆን ሁለተኛው የማሳወቅ ዴስክ በሚል ተሰይሟል፡፡ በመሪ ስራ አስፈጸሚው የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይከናወናሉ፡፡

የማሳወቅ ተግባራት
  • ማንኛውም አዮን ፈጣሪ ጨረራ አመንጪ ቁስ/መሣሪያ በማዕድን መልክ ለማውጣት ወይም ለመፍጨት፣ ለማምረት፣ለመስራት ወይም ለመገጣጠም፣ለማቀነባበር፣በባለቤትነት ለመያዝ፣ለማስተላለፍ፣ወደ አገር ለማስገባት፣ወደ ውጭ ለመላክ፣ለማከፋፈል፣ለመሸጥ፣ ለማዋስ፣ለማከራየት፣ለማከማቸት፣ጥቅም ላይ ለማዋል፣ ስራ ለማቆም፣ለመጠገን ወይም ለመፈታታት፣ለማጓጓዝ፣ ለማስወገድ የሚቀርቡ ማመልከቻዎች በመገምገም/በመመዘን የጨረራ አመንጪዎችንና ተግባራት የተፈቀዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
  • በማሳወቅ ሂደት ያለፉ የጨረራ አመንጪዎችና ተግባራት የተሟላ መረጃ መዝግቦ መያዝ፣መረጃ መተንተን እንዲሁም ሪፖርት ማውጣት፣
  • የጨረራና ኒዩክሌር ህንጻ ግንባታ ሁኔታ የሚቀርበውን ዝርዝር የከለላ ስሌት(shielding Calculation ) ምዘና ማከናወን፣
  • የጨረራና ኒዩክሌር ህንጻ ግንባታ ሁኔታ በቀረበውና በጸደቀው ዝርዝር የከለላ ስሌት(shielding Calculation ) መሰረት እየተገነባ መሆኑን መከታተል፣
  • የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ስልጠናን ጨምሮ ማካሄድ፣
  • ለቁጥጥር ስራ የሚያገለግሉ ሰነዶችን ማዘጋጀት፡፡
የፈቃድ አሰጣ ሥራዎችን ማከናወን
  • ማንኛውም አዮን ፈጣሪ ጨረራ አመንጪ ቁስ/መሣሪያ በማዕድን መልክ ለማውጣት ወይም ለመፍጨት፣ለማምረት፣ለመስራት ወይም ለመገጣጠም፣ለማቀነባበር፣በባለቤትነት ለመያዝ፣ለማስተላለፍ፣ወደ አገር ለማስገባት፣ወደ ውጭ ለመላክ፣ለማከፋፈል፣ለመሸጥ፣ ለማዋስ፣ለማከራየት፣ለማከማቸት፣ጥቅም ላይ ለማዋል፣ ስራ ለማቆም፣ለመጠገን ወይም ለመፈታታት፣ለማጓጓዝ፣ ለማስወገድ የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ለየተግባሩ የተዘጋጁ የሬጉላቶሪ ቁጥጥር መስፍርቶችን መሟላታቸው ሲረጋገጥ የተለያዩ ዓይነት ፈቃዶችን መስጠት

 

Quick Links
  • About ETA
  • Newsroom
  • Our services
  • Your Comment
  • Partner with us
Contact Infomation

+251 1470 5579/5580

info@eta.gov.et

Bulgaria Mazoria, Addis Ababa, Ethiopia

Copyright © ETA  2022