Bulgaria mazoria, Addis Ababa, Ethiopia
info@eta.gov.et
ETA
Ethiopian Technology Authority
Home
About ETA
Services
Radiation sector
Industrial sector
Resources
ETA Publications
ETA Regulation
Others
News & Events
Latest News
Latest Event
Vacancy
Contact us
የቴክኖሎጂ ዘርፍ ጥናትና ምርምር
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የኒዉክሌርና ራድዮሎጅካል፤ኬሚካል፤ኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪካል፤ፕላንትና ማሽነሪ እና ማትሪልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂዎች ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ በህብረተሰቡ፣በአካባቢና በንብረት እንዲሁም በአሁኑና በመጪዉ ትዉልድ ላይ አሉታዊ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳያስከትሉ አስተማማኝ የቴክኖሎጂ የቁጥጥር መሰረተ መዋቅር ለመዘርጋት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ለቁጥጥር መስፈርቶች እንዲሁም ለህግ ማስፈጸም የውሳኔ ሃሳብ የሚረዱ ማስረጃዎችን በቤተሙከራ ትንተና እና ጥናትና ምርምር በማድረግ በማስረጃ የአሰራር ስርዓቶችን በማሻሻል ቴክኖሎጂው የሚያስገኘውን ዘላቂ አገራዊ ልማት ማሳደግ ነው፡፡ እሰካሁን በኒዉክሌርና ራድዮሎጂካል የቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቻ የቁጥጥር ስራ ተዘርግቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ሲሆን በሌሎቹ ዘርፎች ስርአት ዘርግቶ ቁጥጥጥር ከማድረግ አንጻር በኬሚካል ቴክኖሎጂ ላይ ስርአት ለመሰርጋት የተጀመሩ ስራወች ቢኖሩም በሌሎቹ ላይ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲስ ሰራተኞችን ለመቅጠር አቅጣጫ ስላልተሰጠ የተጀመረ ስራ የለም፡፡
በቴክኖሎጂ ጥትና ምረርምር መሪ ስራ አስፋጻሚ የሚመሩ የቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር፤ የራዲዮ አናሊቲካል ላብራቶሪ እና የኬሚካል ላብራቶሪ ዴስኮች የተደራጀ ነዉ፡፡ የባለስልጣኑን በቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ያለዉን ዕቅድ መሰረት በማድረግ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሲዉል የጎንዮሽ ጉዳት እንዳያስከትል የሚደረገዉን የቁጥጥር ስራ ዉጤታማ የሚያደረጉ የምርምር ስራወች ያከናዉናል፡፡ የሬጉላቶሪ ቁጥጥር ስራዉን ከአለም አቀፍ ደረጃወች ጋር የተጣጣመ ለማድረግ የሌሎች አገሮች ላይ የዳሰሳ ጥናት በማድረግና ጥሩ ተሞክሮዎችን በመቀመር ከአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ እንዲሆን ያድርጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከላይ በተገለጹት የቴክኖሎጂ ዘርፎች በአለም አቀፍ ደረጃ ውጤታማ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እንዲለዩና ከሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣሙ በማድረግ ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ እና ጥቅም ላይ ሲዉሉ የቁጥጥር ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን በበላይነት የማስተባበር ስራ ያከናዉናል፡፡ቴክኖሎጂወቹ በስፋት ለልማት እንዲውሉ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ጥናትና ምርምሮችን በጋራ ያከናዉናል፡፡ከዚህም ባሻገር የቴክኖሎጂ የምርምር ስታንዳርዶች ፕሮቶኮሎች፤ የቁጥጥር መስፈርቶችን፤ደንቦችን እና መመሪያዎችን ያዘጋጃል፡፡ በተጨማሪም የባለስልጣኑ የሬጉላቶሪ የአሰራር ስርአቶችን በየጊዜዉ በመገምገም በሚሻሻሉበት ሁኔታ ላይ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
የባለስልጣኑን የቁጥጥር ስራ በመረጃ በማስደግፍ ዉጤታማ ለማድረግ የራዲዮ አናሊቲካል እና የኬሚካል ላብራቶሪወች የተደራጁ ሲሆን የራዲዮ አናሊቲካል ላብራቶሪዉ መሰረተ ልማት ተሟልቶ በሰራ ላይ ቢሆንም የኬሚካል ላብራቶሪዉ ከአዲሱ የባለስልጣኑ አደረጃጀት ጋር የተሰጠ ኃላፊነት በመሆኑ እስካሁን ተግባር ላይ አልዋለም፡፡ የራዲዮ አናሊቲካል ላብራቶሪዉ በአገሪቱ የጨረራና ኒውክሌር ቴክኖሎጂ በሃይል አቅርቦት፣ በኢንዱስትሪው ፣በጤና፣ ግብርና፣ በትምህርትና ጥናት ዘርፍ አገልግሎት ሲውል በአካባቢ፣በህብረተሰብና ንብረት ላይ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳያስከትል ወደ አገር ወስጥ በሚገቡ የተመረጡ የፍጆታ ምርቶች ፣በአፈር ማዳበሪያ፣የማዕድን ልማት ከሚከናወንባቸው ቦታዎች ፣ከታላላቅ የውሃ አካላት ናሙና በመሰብሰብና በቤተ ሙከራ ፍተሻና ትንተና በማድረግ በዘርፉ ለሚደረጉ ጥናት ምርምር ፍተሻና ትንተና በማከናወን ለሬጉላቶሪ ቁጥጥር ስርዓት ዝርጋታ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጨረራ ምክንያት ለሚፈጠሩ የአካባቢና ምግብ ብክለትና ተያያዥ ችግሮች ሲያጋጥሙ ለባለድረሻ አካላት እና ለህብረተሰቡ ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በማዕድን ማውጣትና ልማት ተግባራት በሚያከነውኑ ተቋማት ውጤታማ የአካባቢ ጨረራ መጠን ከትትልና ቁጥጥር መደረጉንም መረጃወችን በመተንተን በጥናት ያረጋግጣል፡፡ በአገሪቱ በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ አላስፈላጊ ጨረራ ወደ ከባቢ አየር ሲገባ የጨረራ ይዘት መጠን መከታተያ ክርስታሎችን በመትከል የተሰበሰቡ የክርስታል መረጃወችን በቤተ ሙከራ በመተንተን ህብረተሰቡንና አካባቢን ከጉዳት እንደጠበቅ ያደርጋል፡፡
የኬሚካል ላብራቶሪዉ አገልግሎት ሲጀምር የኬሚካል ቴክኖሎጂ በኢንዱስትሪው ፣በጤና፣ ግብርና፣ በትምህርት፤ ጥናትና ምርምር ጥቅም ላይ ሲዉል በአካባቢ፣በህብረተሰብና ንብረት ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ሳያስከትል ለዘላቂ ሃገራዊ ልማት ለሚያበረክተው አስተዋፅኦ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዘርፉ አገልግሎት ላይ ከሚውልባቸው ተግባራት ናሙና በመሰብሰብና ፍተሻና ትንተና በማድረግ ለሚደረጉ ጥናት ምርምር ስራወች ለመረጃ ግብዓትነት የሚረዱ የትንተና ውጤቶች በማዉጣት የዘርፉን የሬጉላቶሪ ቁጥጥር ስርዓት ያሳልጣል፡፡ ከላይ በራድዮአናሊቲካል ላብራቶሪዉ የሚከናወኑ ተግባራት ዘርፉን የሚመለከቱ ስራወችን በተመሳሳይ ሁኔታ ያከናዉናል፡፡