Bulgaria mazoria, Addis Ababa, Ethiopia
info@eta.gov.et
ETA
Ethiopian Technology Authority
Home
About ETA
Services
Radiation sector
Industrial sector
Resources
ETA Publications
ETA Regulation
Others
News & Events
Latest News
Latest Event
Vacancy
Contact us
የጨረራና ኒዉክሌር ቴክኖሎጂ የሬጉላቶሪ ቁጥጥር ስራ አስፈጻሚ የሚያከናውናቸው ተግባራት
የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 እንዲሁም የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን አደረጃጀት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው የሚኒስተሮች ደንብ ቁጥር 507/2014 የተቋቋመ ተቋም ሲሆን የጨረራ እና ኒውክሌር ቁሶችንና መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር በአዋጅ ቁጥር 1025/2009 ዓ.ም. በተቀመጡ ድንጋጌዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ ባለስልጣን መ/ቤቱ ያወጣቸውን የቁጥጥር መስፈርቶች ተግባራዊ መሆናቸውን ወይም መሟላተቸውን በማረጋገጥ ህብረተሰቡን፣ አካባቢንና የመጪውን ትውልድ ከጨረራ ጠንቅ ለመከላከልና ለመጠበቅ ስልጣን የተሰጠው ተቆጣጣሪ ተቋም ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 507/2014 በተሰጠው ስልጣንና ተግባር የጨረራና ኒዉክሌር ቴክኖሎጂ የሬጉላቶሪ ቁጥጥር ስራ እንዲያከናውን በ4ዴስኮች የተቋቋመ ሲሆን የኒውክሌር እና የጨረራ አመንጭ መሳሪያዎችንና ቁሶችን ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ፤ ከሀገር ሲወጡ፤ ጥቅም ላይ ሲውሉ፤ ሲጓጓዙ፤ ሲወገዱ፤ ሲዘዋወሩ፤ ሲከማቹ የቁጥጥር፤ ህግ የማስፈጸም፤ እና የክትትል ተግባራትን ያከናውናል፡፡
የጨረራና ኒዉክሌር ቴክኖሎጂ የሬጉላቶሪ ቁጥጥር ዋና ስራ አስፈጻሚ ስር የሚገኙ ዴስኮች በዝርዝር የሚያከናውኗቸው ተግባራት እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡
የጨረራና ኒኩሉየር ቴክኖሎጂ ሴፍቲ ኢንስፔክሽን ዲስክ
የሴፍቲ ኢንስፔክሽን ዲስክ ባለስልጣኑ ያስቀመጣቸውን የቁጥጥር መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ የጨረራ አመንጪ ቁሶች እና መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ሲውሉ ፣ሲዘዋወሩ፣ሲከማቹ፣በማዕድን መልክ ሲወጡ በህብረተሰቡ በአካባቢ እና በንብረት ላይ አሉታዊ ጽዕኖ እንዳያስከትሉ በህክምና/በሜዲካል ፡ በኢንዱስትሪ ፤ በጥናት እና ምርምር፡ በሚጠረጠሩ ቦታዎች፤ የብረታ ብረት አምራቾች እና አቅላጮች እና በማዕድን አልሚዎችና ጥልቅ ዋሻዎችና የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ላይ የቁጥጥር ሥራ ያከናውናል፡፡
የሴፍቲ ኢንስፔክሽን ዲስክ ዋና ዋና ተግባራት እና የቁጥጥር ፕሮግራሞች የሚከተሉትን ተግባራት ያካትታል
በመደበኛ የራጅ መሳሪያ የደህንነት እና የማሽን ጥራት (Performance) የቁጥጥር ተግባራትን ማከናወን
ማሞግራፊ (የጡት) የራጅ መሳሪያ
ሲቲ ስካን የራጅ መሳሪያ
በኢንተርቪንሽናል የራጅ መሳሪያ
ራዲዮ ቴራፒ ማዕከል (ሜዲካል ሊኒዬር አክስሌሬተር)
ኑኩለር ሜዲስን ማዕከል
ኢንዱስትሪያል ጌጆች
ዌል ሎጊንግ
ያላጥፌ ፍተሻ NDT
ትምህርት ጥናትና ምርምር የሚያገለግሉ ቆሶች
የብረታ ብረት ምርቶች ላይ
በብረታብረት አቅላጭ
በሚጠረጠሩ ቦታዎች ላይ
በማዕድን ልማት
የጨረራና ኒኩሉየር ቴክኖሎጂ ሴፍቲ ኢንስፔክሽን ዲስክ
የጨረራና ኒዉክሌር ቴክኖሎጂ የሕግ ማስፈፀም ዴስክ
የባለስልጣኑን ስልጣን፣ ኃላፊነት እና ተልዕኮ እውን ለማድረግ ባለስልጣኑ ባስቀመጠው የሕግ ማስፈፀም ቅደም ተከተል ወይም ፕሮሲጀር መሰረት የጨረራና ኒዉክሌር ቴክኖሎጂ አመንጪ ተግባራትን
በህግ እና ደንብ መሰረት እያከናወኑ መሆኑን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣ የተቀመጠለትን ህግ እና ደንብ ያስከብራል በዚህም መሰረት
የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
የጨረራና ኒዉክሌር ቴክኖሎጂ አመንጪ መሳሪያዎች እና ተግባራት የቁጥጥር መስፈርቶች መሟላተቸውን እና የህግ ጥሰት መኖሩን ይለያል፤
የጨረራና ኒዉክሌር ቴክኖሎጂ አመንጪ መሳሪያዎች እና ተግባራት የተጓደሉ የቁጥጥር መስፈርቶችን እና የህግ ጥሰት ይገመግማል፤
የተጓደሉ የቁጥጥር መስፈርቶች እና የህግ ጥሰቶች የደህንነት ስጋትነት ደረጃን መለየት እና ተገቢ የሆነውን የህግ ማስፈፀም እርምጃን መወሰን ወይም ማስቀመጥ፣
የተጓደሉ የቁጥጥር መስፈርቶች እና የህግ ጥሰቶች የደህንነት ስጋትነት ደረጃን መለየት እና ተገቢ የሆነውን የህግ ማስፈፀም እርምጃን መወሰን ወይም ማስቀመጥ፣
የህግ ማስፈፀም ቅድመ ውሳኔ ውይይት ማድረግ
ተገቢውን የህግ ማስፈፀም እርምጃ መወሰን፤
(የህግ ጥሰቱን ደረጃ መለየት እና የህግ ማስፈፀም እርምጃ መውሰድ)
የህግ ጥሰት ፈፅሞ እርምጃ የተከናወነበት ተግባር ማስተካከያ አድርጎ ሲገኝ የተወሰደውን እርምጃ መሻር፤
የህግ ማስፈፀም እርምጃው ህዝብ ማወቅ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ በባለስልጣኑ የበላይ ኃላፊዎች ውሳኔ ወሰረት መረጃው እንዲሰራጭ ይደረጋል፤
የሲኩሪቲና ሴፍጋርድ ኢንስፔክሽን ዲስክ ተግባራት
የሲኩሪቲና ሴፍጋርድ ኢንስፔክሽን ዲስክ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሃገሪቱ የጦር መሳሪያ ለማምረት የኒውኩለር ቁሶችን ላለመጠቀም በፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ያሉ ግዴታዎች መከበራቸውን በኢንስፔክሽን ማረጋገጥ ነው እንዲሁም የኒውክሌር ቁሶችንና ከፍተኛ የጨረራ አመንጪ ቁሶች/መሳሪያዎች አካላዊ ጥበቃዎች መተግበራቸውን በኢንስፔክሽን ተግባር ያከናውናል፡፡
የሲኩሪቲና ሴፍጋርድ ኢንስፔክሽን ዲስክ ተግባራት እና የቁጥጥር ፕሮግራሞች በሚከተሉት ተግባራት ብቻ ያልተገደቡ ናቸው፡፡
የኒውክሌር ቁሶችንና (ዩራኒዬም፣ፕሎቱኒዬም) እና ከፍተኛ ጨረራ የሚያመነጩ በምድብ አንድ እና ሁለት የሚመደቡ የጨረራ አመንጪ ቁሶችን እና ተግባራትን የሲኩሪቲና ሴፍጋርድ ኢንስፔክሽን ስራ ማከናወን
የራድዮአክቲቭ ዝቃጭ ማቀነባበሪያ እና ማከማቻ ማዕከል፤
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ ማለት የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱና በቀጣይ ምንም አይነት ጥቅም ወይም አገልግሎት ሊሰጡ የማይችሉ፤ ወይም በህገወጥ ዝውውር የተያዙ፤ ጠፍተው የተገኙ፤ ባለቤት አልባ የሆኑ ወይም ተሰርቀው የተገኙ የጨረራ አመንጭ ቁሶች ወይም መሳሪያዎች ማለታችን ነው፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ 2007ዓ.ም ጀምሮ በስሩ የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭን ለማቀነባበር እና ለማከማቸት የሚያስችል ማዕከል ገንብቷል፡፡ ማዕከሉ የተቀነባሩም ሆነ ገና ወደፊት የሚቀነባበሩ የጨረራ አመንጭ ቁሶችን ለማከማቸት የሚያገለግሉ ክፍሎች፤የማቀነባበሪያ ክፍል፤ እንዲሁም የተለያዩ ቢሮዎች አሉት፡፡
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ ከየት ይመነጫል?
በሀገራችን ኢትዮጵያ የጨረራ አመንጭ ቁሶች በዋናነት በህክምናው ዘርፍ፤ በሽታን ለይቶ ለማወቅና በተለያዮ የምርመራ ዘዴዎች ተለይተው የታወቁ በሽታዎችን ለማከም ብሎም የህክምና መሳሪያዎችን ሰቴሪላይዝ ለማድረግ ያገለግላል፡፡ በሌላ በኩል የጨረራ አመንጭ ቁሶች በኢንድስትሪው ዘርፍ ማለትም በመንገድ ግንባታ (የአፈርን የርጥበት መጠንና የአስፋልት ጥራት)፣ በመጠጥ ኢንድስትሪዎች፤ በስሚንቶ ፋብሪካዎች፤ በማዕድን ፍለጋ፤ እና በመሳሰሉት እንደ ሀገር በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በግብርናና በምምርና ጥናት ዘርፍም አገልግሎቱ ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የተረጋገጠ ነው፡፡
ከዚህም በመነሳት የራድዮአክቲቭ ዝቃጭ በዋናነት ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ዘርፎች ይመነጫል፡-
ከጤናው ዘርፍ
ከኢንድስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ
ከግብርናው ዘርፍ
ከምርምና ጥናት ተቋማት
በህገወጥ ዝውውር የተያዙ
ከብረት አቅላጭ ኢንድስተሪዎች እና ሌሎችም
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ አስተዳር ስራዎች ማከናወን ለምን አስፈለገ?
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን በዋናነት፡-
ማህበረሰቡን ተገቢ ካልሆነ የጨረራ መጋለጥ ለመከላከል፤
አካባቢን ከአለ አስፈላጊ የጨረራ መጋለጥና አደጋዎች ለመከላከል፤
ያሁኑንና የወደፊቱን ትውልድ በጨረራ አማካኝነት ከሚመጡ የጤና ጠንቆች እና አደጋዎች ለመታደግ/ለመጠበቅ፤
ሀብትና ንብረትን ብሎም ማህበራዊ ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ እንዲኖር ለማስቻል ይረዳል፡፡
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ አስተዳደር ስራ መሰረታዊ መርሆዎች፤
እንደ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ አስተዳር ስራ በዋናት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መሰረታዊ መርሆዎች ለማሳካት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራ ስራ ነው፡-
የi. የሰው ልጆችን ጤና ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ ካልተገባ የጨረራ መጋለጥ መከላከል (Protection of human health)
(ይህም ሲባል የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ አስተዳር ስረ ሲሰራ የሰዎች የጤና ጠንቅ ሊሆን በማይችል መልኩ እና ተቀባይነት ያለው የሰዎችን ጤና ከጨረራ መከላከል የሚያስችል መሆን አለበት፤ )
አካባቢን ከጨረራ መከላከል (Protection of the environment)
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ አስተዳር ስራ ወሰን ተሻጋሪ በመሆኑ ይህንን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ በሰው እና በአካባቢ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ተጽዕኖ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ስረዎች መከናወን አለባቸው፤
ጨረራ በአጭርና በረጅም ጊዜ በሰው ልጆች ጤና ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድርና የከፋ ችግር የሚያስከትል በመሆኑ መጭውን ተውልድ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የጨረራ መከላከል ስራች መከናወን ( Protection of future generations) አለባቸው፤
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ አስተዳር ስራዎችን ለማከናወን ተገቢ የሆነ ብሎም ሃላፊነትንና አቅረቦቶችን በግልጽ የሚያሳይ የህግ ማዕቀፍ እና መሰረተ ልማት (National legal framework) ባሉት ገለልተኛ ተቆጣጣሪ አካል ሊመራ ይገባል፤
የሚመነጭን የራድዮአክቲቭ ዝቃጭ በተቻለ መጠን ዝቅተኛ እንዲሆን በተገቢው መቆጣጠር (Control of radioactive waste generation)
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ መመንጨት እና የአስተዳደር ስራዎች ለየቅል በመሆናቸው (Radioactive waste generation and management interdependencies) የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ የማንጨት እና የራዮ አክቭ ዝቃጭ አስተዳደተር ስራዎች በተናጠል ደረጃ በደረጃ በተገቢው መከናወን አለባቸው፤
የራድዮ አክቲቭ ዝቃጭ አስተዳደር ስራዎችን የሚያከናውኑ ተቋማት ደህንነት በተገቢው መረጋገጥ አለበት፤